በጅማ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የስፖርት ፌስቲቫል ላይ የተሳተፈው የቦረና ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ልዑካን ቡድን በዛሬው እለት በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ጊቢ በመገኘት የፅዳት ዘመቻ በማካሄድ መልካም ተሳትፎን አድርጓል ።
የቦረና ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ልዑካን ቡድንም በጅማ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ሲካሄድ በቆየው የስፖርት ፌስቲቫል ላይ የጅማ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም የጅማ ከተማ አስተዳደር ላሳዩት መልካም አቀባበል እና ፍቅር የተሰማውን ላቅ ያለ ደስታ ይገልፃል ።



የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ


