Registrar

Registrar

ማስታወቂያ

በ2ዐ13 ቦረና ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ

የቦረና ዩኒቨርሲቲ የግንባታ ሥራውን አጠናቀዉ ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎችን ለመቀበል ቀን ቀጠሮ መያዙን በታላቅ ደስታ ያበሰራል፡፡

ውድ ተማሪዎቻችን! ዩኒቨርሲቲያችንና የአከባቢው ማህበረሰብ ሊቀበላችሁ ዝግጅቱን በመጨረስ ላይ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን ነሐሴ 27 እና 28 /2013 መሆኑን አዉቃችሁ ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ስትመጡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የትምህርት ማስረጃዎችና ቁሳቁሶች ይዛችሁ መምጣት እንደሚጠበቅባችሁ እናስገነዝባለን፡፡

የ8ኛ፣የ1ዐኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናዉና ኮፒዉን
ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የተማራችሁበትን ትራንሰክሪፕት ዋናዉና ኮፒዉን
3 በ 4 ፎቶ ግራፍ (ብዛት 8)
አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የስፖርት ትጥቅ እና የትራስ ልብስ
የኮቪድ-19 መከላከያ አፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል (ማክስ)
ማሳሰቢያ

ከተጠቀሱት ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣዉን የማናስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲዉ ያሳስባል፡፡ ለበለጠ መረጃ የሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክተርን ቀጠሎ በተጠቀሱት አድራሻ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

የእጅ ስልክ፡ ዐ939925599

e-mail:- Mhargesa@bru.edu.et

ቦረና ዩኒቨርሲቲ